Fawners

           Fawners

Compromising your stance

You may meet ends

At once,what a chance!

 

Go join enjoy their farce,

So called democracy’s dance.

 

But yourself from yourself

You will distance,

Worse losing integrity or balance,

You are sure

To experience

A lapse,

In to moral decadence

It is an era for the survival of

The slickest,

Not the fittest.

 

You are cutting the branch

From the tree yourself

Your country to detach.

Advertisements

እዳ

                እዳ

 

በደንብ ጠበቅ አድርገህ ላፈቀርከኝ፣

የምከፍለው ምን ወሮታ አለኝ?

 

ለነፍሴ ክንፍ አለገስካት፣

ለልቤም መዝሙር አልሰጠሓት!

 

ግን ውይ ለወደድኩት

ላላፈቀረኝ ፣እዳ አለብኝ፣

በሩን  ልከፍት፣

በግርግዳው አርጎ ሠተት፣

የሚያዘልቅ ወደገነት!

 

(በሳራ ተሰዳለ፣ትርጉም  ዓለም ኃይሉ )

ልቤ ከብዷል

        ልቤ ከብዷል

እንዳጎነበሰ ዛፍ የበሰለ ፍሬ አግቶ፣

ሌቤ ከብዷል በመዝሙር ተሞልቶ፡፡

 

ግን አንድ በፍፁም፣ልሰጥህ አልችልም፣

መዝሙሮቼ የኔ አይደሉም!

 

ሆኖም በጠፍ ጨረቃ ማታ፣

ነፍሳት ሲወራጩ ከቦታ ቦታ፣

በግራጫማዋ ሠአት፣

ፍሬ ከወደቀ ምናልባት፣

ውሰድ-ማንም አያውቅም!

 

(በሳራ ተሰዳለ፣ ትርጉም ዓለም ኃይሉ)

Great Tiding

Great Tiding

Blue Nile echo from shore to shore,

“Poverty in Ethiopia is no more!”

Above all,

From a precipice

       To a valley when you majestically fall,

Thunderous over

The damp dell, mountain gorge when you roll,

As usual

With green, yellow and red

Rainbow arched,

Tell Ethiopia loud-

“You children thee very much adore,

A lip service they now abhor!

‘Blue Nile has no lodging,

Yet it loafs a log hauling.’ ”

Blue Nile, about your deeds to talk

Breathtaking, you served well

The industry without smoke,

But now you have an extra work!

Far

       And

                Wide

Ethiopia will be electrified,

With Blue Nile,

                       Gebe,

                             Tekeze… at hand!

Every nook and cranny will get light,

When efforts Ethiopians unite!

The future will be bright,

When a tamed Blue Nile ceases

Unchecked to roar past

Without a respite.

No energy source runs waste

Nor any Plant will suffer a blackout!

Lo and behold Blue Nile will be subdued

For riparian countries’ good!

To contribute a brick,

Ethiopians twice you shouldn’t think.

 

Farmers have mounted on a peaceful battle,

To cover the catchment with a green mantle,

To make terrain

                          On each mountain

Take every pain.

To afforest the depleted f o r e s t!

Thus washing on its sway,

Blue Nile conspires no more

To carry alluvial soil away.

Here of course it is good to recall

The message of Emperor Twedrose.

Dear guests you are

Amidst people hospitable

Welcome, welcome

Feel at home!

Roam throughout

Abyssinia you might,

On its grandeur your eyes

You can feast.

The vast array of

Mouthwatering dish,

The country parades

You could relish.

In case you wish

For an adventure,

Still Ethiopia

Is a mosaic of culture!

Of course

It will grab your attention,

Ethiopia’s being

A cradle of mankind

And ancient civilization.

You will see

To its music titillating,

Comes close nothing!

Moreover fails not

To draw your attention,

The affection

Among people hailing from

Different nationalities  and religion.

But you can’t transport a speck of dust,

Alighted or pasted on your shoe by accident!

So to get an exit,

Shake off your shoe and wash your feet!”

 

Giving to every dust attention

It is possible to ward off

The problem of siltation.

Besides don’t you think

The forests serve a carbon sink?

 Blue Nile echo from shore to shore

“Poverty in Ethiopia is no more!”

As though Abyssinia,

Africa’s water tower

Is a weakling with no power,

On every news hour,

Portraying Ethiopia

A development backwater,

Also scornfully on a dictionary

Painting its people thirsty and hungry

Have no grounds any!

From a rain fed agriculture

Head on

Making a paradigm shift,

Irrigation when Ethiopia further adopt,

The vicious cycle of drought,

Which pose a threat

To its development,

Will give way to a bumper harvest,

Once more rendering Ethiopia

A  cornucopia.

 

Ethiopians be not cool,

Be not cool

Resources to pool!

Lo and behold Blue Nile will be subdued

For riparian countries’ good!

 

Yet, yet hanging up together

Be high on the alert

Any aggressor to deter!

Many are

Who wear a frowning face,

When development

In Ethiopia picks pace!

Keep open your eyes,

Keep open your eyes

At all time, all space

Where infrastructures

Are put in place.

 

To the helm of development

Ethiopia will soon catapult,

When its children

In full harness their resources put.

So cognizant of this fact,

Ethiopians allow not

The grass to grow under your feet.

Don’t wait

Behind the campaign

To throw your full weight!

 

For work, roll up your sleeve

Ready for ‘The Renaissance Dam’

Your sweat

 

  B

 L

   O

O

    D

And life to give.

March out for prosperity

In Ethiopia to thrive,

What we need have

Is a bond-cohesive

B-O-N-Decisive.

Go all out, go all out,

Us, lucky we have to count

For seizing such a ripe moment.

 

 Blue Nile echo from shore

“Poverty in Ethiopia is no more!”

Come-on let us not beg to differ,

Of course we could concur,

For all of us will agree,

Our pet dream is to see,

Ethiopia industrialized

Completely transformed!

Laying the foundation,

Where on takes off

The future generation,

Is what begs for

Central attention.

 

Why, Why and Why,

With our hands

Tucked in our pockets,

You and I

Remain standers by?

Also why

Simply watch the clouds

Glide across the sky?

Must we indeed,

Sowing a discord seed

Allow our rivers run wild,

Turning a blind eye to our need.

 

Wiseacres, though

You may not be on the same page,

Between stakeholders

Don’t drive a wedge,

The government proves out

Out to fulfill its pledge.

 

In life it is not hard

To get skeptics,

Dear leaders talk your walk

Walking your talk!

Prove skeptics wrong

Letting them witness

The actualization

Of the dam agog.

 

Tax payers, if you have

A tax arrear

See it finds its ways to

The government’s coffer.

 

Taxes being

A development backbone

Must be mysterious to none.

Target  also rent seekers

That drive spokes

In to development wheels.

By AlemHailu(alemhailu2007@gmail.com)0911922895,   M.A in  Literature,www.alemhailugk2007.wordpress.com

 

 

ቀበጧ ፅጌረዳ

           ቀበጧ ፅጌረዳ

እንቡጥ ፅጌረዳ አንገቷን ሰገግ አርጋ፣

ብቅ አለች ከአትክልቱ ሥፍራ በአበቦቹ አልጋ፣

አፍላ የወጣትነትን ወራት፣

የሚያጅበው የትኩስ ደም  ኩራት፣

በቃ አፍነከነካት!

ከጎኗ አትክልተኛውን ቆሞ ስታስተውል፣

የሃሳብ ብርቅታ ኣላት ውል-

‹‹አርጅቷል-በጣም አርጅቷል

በቅርቡ ይሞታል!››

 

ሞቃታማው የበጋ አየር ስለተስማማት፣

ክንፎቿን ዘርግታ በስፋት፣

ምንም ለመደበቅ ሳትዳዳ፣

ከፈተች የልበቧን ጓዳ!

ስትሰማ የእግሩን ኮቴ እንደገና

አሳቃት ደና- ‹‹አርጅቷል፣ አፍጅቷል

ብዙ ሰንብቷል አሁንስ ይሞታል!››

 

ግና የማለዳው ንፋስ ደርሶ፣

ስፍራውን አተራምሶ፣

ሲሄድ ተጣድፎ

አስተዋለ የፅጌረዳ ክንፍ

በአትክልቱ ቦታ ተነስንሶ!

 

ቀትር ላይ አዛውንቱ አትክልተኛው፣

ሁሉንም በሹካው፣ሰብስቦ ከላው!

 

እናም በዚህ ጉዳይ ስለተመሰጥኩ፣

የስንኝ ቋጠሮ ከተብኩ!

 

እኔ እንደአስተዋልኩት

ፅጌረዳዋ የውበትን

አትክልተኛው የጊዜን

ምስል ነው የሚከስቱት

 

(በአውስቲን ዶብሶን፣ትርጉም ኣለም ኃይሉ, ከፎንቴሌ የተወሰደ)

 

ረጅም ጦር ባይወጉበት ያስፈራሩበት!

                  ረጅም ጦር ባይወጉበት ያስፈራሩበት!

‹እንደአንቺ አላየሁም እስከአሁን—› የሚለው ሙዚቃ ከሆቴሉ አንድ ጥግ ከተሰቀለ የልብስ ሳጥን ከሚያህል ሞንታርቦ ያስገመግማል::

አንድ ኮረዳ ከሴት ጓደኞቿ ጋር አብራ እየደነሰች ‹‹አቦ ይመቸን! አቦ ላፍ!›› ትላለች፡፡

ደናሾቹ  እንደ እባብ የመተጣጠፍ ብቃታቸውን ለማሳየት እንዲሁም ገላቸውን ለማስመረቅ  ይወዛወዛሉ፡፡ ጀማሪ የሆኑት ደግሞ ‹እንቅስቃሴዎች ሁሉ ዳንሶች ናቸው!› የሚለውን ይዘው ይወራጫሉ፡፡

ጽጌረዳ ዓይነ ባትሪ የደምገንቦ ኮረዳ ናት፡፡ ጎረድረድ ብትልም መቀመጫዋን በግሩም ሁኔታ አቅፎ የያዘው ሰማያዊ ስስ ሱሪዋ እና የጠቦት ቀንድ ጡቶቿን በከፊል የሚያሳየው ቀጸላወርቅ ቲሸርቷ ተባብረው ጉደኛ ቅርጿን አጉልተው በዙሪያዋ ያሉ ሴቶችን መስህብ አጠይመው ቸበርቻቻ ከሚበዛባቸው ከካዛንችስ ሆቴሎች አንዱ ከሆነው ጭፈራ ቤት የወንድ ዓይን የምታስቀር የወሲብ ጣኦት አንድትሆን አድርገዋታል፡፡ ልጅነቷና ተጫዋችነቷ ከሳቢ ቅርጿ ጋር ተዳምረው በሆቴሉ አዘውታሪ ጠጪዎች ፊት ተጋባዥነቷንና ተዘውታሪነቷን አንረውታል፡፡

አንድ ሁለት ለማለት ፀሃይ ስትጠልቅ ወደ ቡና ቤቱ ጎራ ያለ ወንድ በቤተሰብ እንክብካቤ ማደጓን የመጎዳት ምልክት ከማይነበብበት ሠውነቷ ሲያነብ ‹ይቺን የመሰለች ልጅ እንዴት የቡና ቤት ህይወት ጀመረች› ብሎ ራሱን መጠየቁና ቶሎ ሊወዳጃት ማሰቡ አይቀርም፡፡

የሉል ቅርጽ ያለው፣ ባለብዙ መስኮት የኳስ መነጽር ያጠለቀና እየተሸከረከረ የህብረቀለማት ጨረር የሚረጨው አምፑል ከወገባቸው በላይ መስታወት የተገጠመላቸውን ግድግዳዎች እንዲሁም የእምነበረድ  የወለል ሸክላዎች በብርሃን ዘሃዎች ሲዳብሳቸው ብርማ ቀለበቶችና  ወርቃማ ኮከቦች የተርከፈከፈባቸው ይመስላል፡፡ ተዝናኚዎች በየጥጉ ተመስገው ከዓይን ተሰውረው ሙዚቃውና የህብረቀለማት ጨረሩ በሚፈጥሩት የመዝናናት መንፈስ በውስኪ፣በቢራና በድራፍት ሞቅታ ወደሌላ ዓለም ተሳፍረው ‹አንድ ወንድ ለአንድ ሴት፣ ለአንድ ምሸት!› የተባለ ይመስል ጥንድ ጥንድ ሆነው በየጥጉ ተጠጋግተው ያወራሉ፣ ጥንድ ጥንድ ሆነው በኋለኛው በር ሹልክ እያሉ በጠባብ ደረጃ ሽቅብ ተረማምደው ግራውንድ ፕላስ ዋን ከሆነው የሆቴሉ ህንፃ ላይ ወዳለ ቤርጎ ያቀናሉ፡፡

መክብብ መነሻው ምን እንደሆነ በማያውቀው ምክንያት ከልጅነት ጀምሮ የተፀናወተውን የሻጉራነት ባህሪ ለአፍታ የሚገላገለውና ከአነስታይ ፃታ ጋር ፍቅር መሳይ ስሜት የሚያጣጥመው ዓይንአፋርነቱን የድራፍት ብርጭቆ ውስጥ ሲረፍቀው ነው፡፡

ጊዜአችሁን ከእሁድ አስከ እሁድ ከጠዋት አስከማታ ሰዉልኝ በሚለው በቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት ሥራ ላይ ስለተሰማራ በሚያገኛት አጋጣሚ ማታ ቤት ከመግባቱ በፊት፣ ሙሉ አዲስ አበባ ሲያንቀላፋ፣ ብልጭ ድርግም በሚሉ አንጸባራቂ አንፑሎች ተሸልመው እጅ ለእጅ ተያይዘው በሚሰየሙ ባለፍሬንች ዊንዶ የካዛንቺስ ጭፈራ ቤቶች ትንሽ ለመጎንጨት ጎራ የሚለው፡፡

የደመወዝ ሰሞን ደግሞ ለቤተሰቦቹ ፊልድ እንደወጣ ተናግሮ ቀልቡ ከወደዳት ሴተኛ አዳሪ ጋር አንሶላ ይጋፈፋል፡፡ከአንድ ደንበኛ ይልቅ ከአንዷ ወደ አንዷ እያለ ሴት አንደሸሚዝ እየቀያየረ አለ፡፡

ማታ ከሥራ መልስ አንድ ሁለት ለማለት ሠራተኞችን ቤት የሚያደርሰውን ሹፌር ካዛንቺስ ባቢሎን ህንጻ አካባቢ

‹‹እዚጋ አውርደኝ!›› ብሎ ከህንጻው ሥር ከተደረደሩት አንደኛው ጭፈራ ቤት ዘው አለ፡፡ ግማሽ ግማሽ  ድራፍት የቀራቸው ብርጭቆዎች የሚስተዋሉበትና በግራና በቀኝ ሁለት ባልተያዙ ወንበሮች የታጀበ ጠረጴዛ አየ፡፡ ይህ ጉዳይ ሁለት ጥንዶች ተያይዘው ወደማረፊያ ክፍል ሹልክ ማለታቸውን አሳበቀለት፡፡ በሌላ ጠጪዎች ሳይቀደም ቀጥታ ወደዛ አቅንቶ ቦታ ያዘ፡፡

ከአስርተ ዓመታት በላይ እዚያ ቤት የሠራች ወገቡ ላይ በነጭ ቀበቶ የታሠረ አጅጌ የሌለው ቀይ ቀሚስ የለበሰች፣  ቀይ ጫማ የተጫማች ቀይ አበባ ያለበት ነጭ ኮፍያ ያደረገች፣ ረዘም ወፈር ያለች አስተናጋጅ በጭንቅላቷ ሠላም ብላው በሰርቪስ ብርጭቆዎችን ሰብስባ ጠረጴዛውን ወልውላ፣

‹‹ምን ላምጣ ? ›› አለችው

‹‹ምነው ተጣደፉ ባክሽ? የድራፍት ጡር የለውም ብለው ነው?››ሲላት

‹‹ተው እባክህ ድራፍት ሲጋቱ ነው ያመሹት፡፡ ጠግበው ነው ይሄን የተውት!››

‹‹ሌላ ነገር እራባቸው?››  

‹‹እንደዛ ነው መሰለኝ! ከልምድ ታውቀው የለ፡፡››

 በጁ ወደኋለኛው በር እያሳየ ‹‹የህይወት ስንቅ ይዘዋል? አደራ እሮጥ ብለሽ ንገሪያቸው፡፡›› ፈገግ ብላ

‹‹ምነው ዲኬቲዎች ናቸው እንዴ የላኩህ? እድሜ ይስጣቸው ይሄው ስንቱ ያልነቃ ሲሸኝ እኔ እንደምታየኝ እስከ ዛሬ አለሁ!››

‹‹አዎ ትገርሚኛለሽ Forewarned is Forearmed ‹ቀድሞ የነቃ ስለታጠቀ አይጠቃ!› ይላሉ ፈረንጆች፡፡ጋዜጠኛ ስለሆንኩ ከዲኬቲና ከሌሎች ኤችአይቪ/ኤድስን ከሚዋጉ ድርጅቶች ጋር ሠርቼአለሁ፡፡››

‹‹አዎ ጋዜጠኛ ነህ! ሁሌ ቦርሳ ደፍተር ይዘህ ነው የምትገባው፡፡ ያ ሲጠጣ የሚለፈልፈው ከበደ አንድ ቀን ‹ምን የሠው ሙድ ይሰርቃል ትምህርት ቤት መሰለው እንዴ!› ብሎ ሲተርብህ በሳቅ ፍርስ አድርጎኛል፡፡››

‹‹ውይ ከበደ ነፍሱን ይማረውና ፡፡ ሑሌ ከአንዱ ቤት ወጥቼ ሌላ ጋ ሥገባ  እሱ ሲወጣ ከተገናኘን ‹በአራተኛው ፔሬድ እንገናኝ!› ይለኝ ነበር፡፡››

‹‹ውሃ ይወድ ነበር ውሃ ወሰደው! ምን የመሰለ መሐንዲስ ነው ሲሉ ሰምቼአለሁ!››

‹‹ለህይወቱ ዋጋ ሳይሰጥ ቀርቶ እንደሆነስ?›› ተሳስቀው

‹‹ኧረሱቴ፣ ሴትን ለተረብ እንጂ ለፍቅር አስቦ የሚያውቅ አይመስለኝም! እኔን እኮ ‹እሜቴ ስምንት ቁጥር!› ነበር የሚለኝ፡፡››

‹‹ እውነቱን ነው ዛሬም ስምንት ቁጥር ነው የምትመስዪው! ጌጤ የተባልሺው ለዚህ አይደል፡፡ አለባበሱን ደሞ ትችይበታለሽ››

ልቧን በአንድ እጇ  ደግፋ‹‹አመሰግናለሁ! አንተም ሰፊ ደረት ግሩም ጥርስ አለህ በዛላይ ቀይ ነህ! ፊልድ ወጥተህ ነው? ሦስት ወር ያልፋል ካየሁህ፡፡››

‹‹አዎ አንድ ሁለቴ ወጥቼአለሁ!››

እየተሸኮረመመች ‹‹የህይወት ስንቅ ይዘህ ነው?›› እንደገና ተሳስቀው

‹‹ያለሱ ጨዋታ አለ ብለሽ ነው!››

‹‹አሁን ምን ይምጣልህ በደረቁ አታድርቀኝ!››

‹‹  ወይ ላንቺ በኋላ በጥሬው ይሰጥሻል፡፡ ድራፍት አምጪልኝ!››

 ከደቂቃ በኋላ ድራፍት ይዛ ስትመጣ

‹‹ያቺ መሐል የምትደንሰው ደሞ ማናት? እኔ ያልመዘገብኳት?››

ጌጤ ዞራ ማየት ሳያስፈልጋት ‹‹ቀሽት የሆነች ልጅ ናት! ሁለት ወር አይሆናትም  እዚህ ከገባች፡፡›› አለች

‹‹ለዚህ ነው ዲጄው እኔ ስገባ ‹ላፍ አርጋት!› የሚለውን ሙዚቃ የቀየረው፡፡›› ተሳሳቁ

‹‹ከአንቀልባ ሾልካ ሳይሆን አይቀርም እዚህ የገባችው፡፡ ሕፃን ትመስላለች!››

‹‹ሕፃን ጋንዲ ነው ያለው! አስራስምንት ከዘለሉ በኋላ ምን ህፃንነት አለ?››

‹‹ስሟ ማነው?››

 ‹‹ጽጌረዳ ነው የምትባለው፡፡››

‹‹ከፈለግክ ጽጌ ብለህ ጥራት፡፡ ግን የቤት ልጅ አገኘሁ ብለህ እንዳትሸወድ፡፡ ከምታምናትና ከምታምንህ ባለቤትህ በቀር ጨዋታው በኮንዶም ነው፡፡ አናዛት፡፡ ብዙ ታሪክ ነው የምትዘከዝክልህ፡፡››

‹‹አንቺ ግን በጣም አስተዋይ ሴት ነሽ፡፡ በአንድ ወቅት ኤችአይቪ በቡና ቤት አካባቢ ብቻ የሚያንዣብብ ችግር ተደርጎ ስለሚወሰድ ኮንዶም በመጠቀም ዙሪያ የመዘናጋት ነገር በመፈጠሩ በርካታ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና የቢሮ ሠራተኞች ከቫይረሱጋ እንደሚኖሩ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶችና መሥሪያቤቶች የተካሄዱ ጥናቶች አንደሚያሳዩ ለማወቅ ችዬአለሁ፡፡››

‹‹የቡና ቤት ሴት ነች! የቤት ልጅ ነች! ሠራተኛ ነች! ላይ ሳይሆን  የትነው የምትሠራው? ላይ ሳይሆን እንዴት ነው የምትሄደው? የሚለውጋ ነው ቁምነገሩ ያለው፡፡ ይሄው እዚህ ቦታ ስንት ዓመቴ በፊት ከኔጋ የነበሩ በጊዜ ያልነቁ ቤትም መሥሪያ ቤትም ያሉ ቀድመው ያላወቁ ወይ ያልተጠነቀቁ አሁን የሉም፡፡ እኔ ግን አለሁ፡፡ በፊት ሌሎች ሴቶችን አልመክርም ነበር፡፡ አሁን ግን ዲኬቲዎች ወይ ሀብኮ ባይከፍሉኝም ‹ያለኮንደም ጨዋታ የለም!› እያልኩ ሁሉንም አስተምራለሁ፡፡ ‹በጥልቅ ወይም በፍሬንች ኪሲንግ ድድ ሊደማ ስለሚችል ኤችአይቪን ጨምሮ ሄፒታይተስ የመሳስሉ በሽታዎች ሊተላለፉ ስለሚችሉ ለሱም ኮነዶም እስኪሠራለት ከንፈራችሁን አትስጡም! ›እላቸዋለሁ፡፡ ››

‹‹ አይዞሽ ከእግዚአብሔር ታገኚዋለሽ! ደሞስ ሌሎችን ማንቃት የዜግነት ሃላፊነታችን ነው፡፡››

‹ከፈለግክ ፅጌንም አስቀድሜ አንቅቼአታለሁ፡፡ቡና ቤት ከሚሠሩ ሴቶች በጓደኝነት ስም ብር የሚቀበሉ ቦይፍሬንድ ተብዬ ጎረምሶችም አሉ፡፡‹ያለ ኮንዶም አንረካም!› እያሉ የረባ መተዳደሪያ ሳይኖራቸው ሴቶቹን  ያስወልዳሉ ወይ የአባለዘር ወይ የኤችአይቪ በሽታ ያሲዛሉ፡፡››

‹‹ኧረ ሶስቱንም ሊያሸክሙ ይችላሉ፡፡››

‹‹ምን እሱ ብቻ የቡና ቤት ሴቶችን፣ የቤት ልጆችንና ሴሰኛ ባለትዳሮችን ያነካካሉ! ሴቶቹ፣ በተለይ ፍንዳታዎቹ እዚህ ቡና ቤት ተጠንቅቀው ሰፈራቸው ይሸወዳሉ፡፡ መስከረምን ታውቃታለህ?››

‹‹ ግንባሯ ላይ ንቅሳት ያለባት!››

 ‹‹በምን አየኸው? በፀጉሯ ትሸፍነዋለች አይደል!››

‹‹ አንዴ አብረን አድረናል!››

‹‹ አዎ ቀማሽ አይደለህ? አንተም ቀድመህ ባትነቃ ይሄኔ …››

‹‹አንዴ ክፍል ለመግባት እንደተስማማን ሂሳብ ተቀብላኝ፣ ስልክ ደውላ፣ ለሆነ  ጠብሻ ጎረምሳ በራፉ ጋ ወጣ ብላ ብር አቀበለችው! ይገርምሻል ልጁን ከብዙ ሴቶች ጋር ነው የማየው››

‹‹ልክ ከሱ ልጅ አርግዛ የሚያርሳት አጥታ ገንዘብ አዋጥተን ደንበኞቿን አስቸግረን ብር ሠጠናት!››

‹‹ሚሚንስ ታውቃታለህ?››

‹‹ሮቶ የምንላት?››

‹‹ አዎ ‹ዶሮ ያርድልኛል፣ ከሠፈር ጉልቤዎች ይጠብቀኛል!› ብላ  የሆነ ጎረምሳ አስቀምጣ እየደጋገመ የሚከሰት የጨብጥ በሽታ አሲያዛት፡፡ ሀኪም ቋሚ ክትትል ያስፈልገዋል ብሏት ይሄን ሥራ እንኳን መሥራት አቅቷት ቤት ቀርታለች፡፡ ሳይመረመሩ ሳይተማመኑ ያለኮንዶም መሔድ ጠንቁ ብዙ ነው፡፡ ››

‹‹‹አዎ ገጠር ወሊሶ አካባቢ ባሎቻቸው በሥራ ምክኒያት ከተማ ቆይተው ሲመለሱ ‹ካልተመረመርክ አብረን አንተኛም!› የሚሉ ሚስቶች መኖራቸውን ሥሰማ ተደንቄ ነበር፡፡ መተማመን ላይ ጥርጣሬ ካለ ትዳር ውስጥ ይሁን ከትዳር ውጭ ኮንዶም መጠቀም ያዋጣል!››

‹‹ ጎበዞች ናቸው!››

‹‹እንደኔ አይነት ጠንቃቆች ደሞ እንዳንተ አይነት ደህና ሠው እያገቡ ይወጣሉ፡፡ አስቴር ክልሷ ሚስቱ የሞተችበት ጠበቃ ጋር ተመርምረው ተጋብታ አሁን ልጅ ሊወልዱ ነው! እዚህ ሲመጣ ነው የተዋወቁት፡፡ እኔም ‹አልጋ ሙሉ ሴት ነው የምወደው!› ከሚል የኢምባሲ ሹፌር ጋር መስመር ውስጥ እየገባሁ ነው፡፡››

መክብብ ‹‹እሰይ መፋቀር ደስ ይላል! ለእንደኔ አይነቱ ዓይናፋር ወንድ መልካም አጋጣሚ ነው፡፡›› ብሎ ልቡ እሷ ጋር ስላለ ሳያስበው ለጽጌረዳ የእጅ ምልክት ሲሰጣት ልብ ስላላለች ዝም ብላ ትደንስ ነበር፡፡

ጌጤ ዞር ብላ ጽጌን አይታ  ‹‹ፈለግካት? ልጥራልህ?››

‹‹እሺ››

ጌጤ ወደ ጽጌረዳ አምርታ በጆሮዋ የሆነ ነገር ነግራት ተያይዘው ወደ መክብብ ጠረጴዛ መጡ፡፡መክብብ ሌላ ያልተያዘ ወንበር አመቻችቶ ጽጌረዳን ከአጠገቡ አስቀመጣት፡፡

ጌጤ ‹‹ፅጌ ምን ላምጣልሸ?›› አለች፡፡

ጥድፍ ብሎ‹‹ ‹ቢራ አምጪላት! ምርጫዋን ታውቂ አደል!› ›› አለ፡፡ 

ጽጌን ስለጠራችለት ውለታ ለመክፈል ያሰበ ይመስል ‹‹ ላንቺ ደሞ ጃንቦ አምጪ!›› አለ፡፡

ጌጤ እንደሔደች መክብብ ጽጌን

‹‹ይሄን የመሰለ ውበት ተሽክመሽ እዚህ እንዴት ገባሽ?››

‹‹ብዙ ወንዶች የሚጠይቁኝን ጥያቄ ነው ያቀረብክልኝ! ግን ያን ያህል ቆንጆ ነኝ እንዴ?››

‹‹የድንግልናዊ ውበትን ጣሪያ የነካች ኮረዳን መስህብ ተላብሰሻል! እርግጠኛ ነኝ ለፍቅር ብለሽ ነው ከቤት የወጣሽው አይደል?››

‹‹በምን አወቅክ? ስለኔ የጠየከው ሰው አለ እንዴ?››

‹‹መገመት ያቅተዋል ብለሽ ነው? አዳዲስ የሚገቡ እንደ አንቺ አይነት ሴቶችን ሁሌ ቃለመጠይቅ አቀርብላቸዋለሁ፡፡ አዎ አንድ ጋዜጠኛ በየቡና ቤቱ እየዞረ ሴቶችን ታሪክ እየጠየቀ ማስታወሻ አንደሚይዝ ሴቶች ክፍል ሲያወሩ ሰምቼአለሁ ፡፡ አንተ እንዳትሆን!››

‹‹እኔ አይደለሁም፡፡ እንዲሁ ለጨዋታ ነው የጠየቅኩሽ፡፡››

‹‹አዎ ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ፡፡ እስከ ዘጠነኛ ክፍል ተምሬአለሁ፡፡ ሁለተኛ ወይ ሦስተኛ ነበር የምወጣው፡፡ የአብነት ሰፈር ልጅ ነኝ፡፡ እዚያ አካባቢ ከፍተኛ አራት ወይ በቅጽል ስሙ ‹አናጋው› የሚባል ትምህርት ቤት ነበር የምማረው፡፡››

የኢንተርኔት ተጠቃሚ ጎግል ውስጥ መረጃ ጠይቆ መረጃው እስኪዘረገፍለት ድረስ በሚያሳየው የጉጉት ስሜት

‹‹ እሺ? ›› አለ

‹‹ አስረኛ ክፍል ስንገባ ከክፍል አለቃችን ጋር ሀይለኛ ፍቅር ውስጥ ገባን፡፡ ጓደኞቼ አስተማሪዎቼ ‹ተይ!› ቢሉኝ ልሰማቸው አልቻልኩም፡፡››

 ‹‹ልክነሽ ‹ፍቅር እውር ነው!› ይባላል፡፡እድሜያችን ሳይበስል የምንገባበት ፍቅር ትንሽ ያጃጅላል፡፡ ህጻን ሳለሁ የቴለቪዥን ዜና አንባቢ አፍቅሬ መጃጃሌ ትዝ ይለኛል፡፡ ዜና ሲነበብ ሁሌ ከፊት ጉብ እል ነበር፡፡› ›ጽጌ ፈገግ አለች፡፡

ጌጤ በመሐል መጥታ ‹‹ይቅርታ ድራፍቱ እየተለወጠ ስለሆነ ነው! የጽጌን ቢራ አምጥቼላታለሁ፡፡›› ብላ ቢራውን ከፍታላት ተመልሳ ሔደች፡፡

 ‹‹ ወጣት እያለህ ሌሎች ስለፍቅር የሚያውቁ አይመስልህም፡፡እንዲያውም የሂሳብ አስተማሪያችን አንድ ቀን አንድ እንቆቅልሽ አይነት መልመጃ ሰጥቶን እየዞረ መልስ ሲያይ መሐል ድረስ ሠርቼ የቆምኩትን ተመልክቶ ‹በደንብ እኮ ነው የሠራሽው! ለምን አልጨረሽውም?› ሲለኝ ወዲያው ጨርሼ አሳየሁት፡፡ ትልቅ ራይት ሰጥቶኝ ‹ጎበዝ ልጅ ነሽ፡፡ መሠረት አለሽ ማለት ነው!› ›› አለኝ፡፡

ደብተሬን ገለጥ ገለጥ እያደረገ ሲያይ ‹የፍቅር ማደሪያ› የሚል ጽሁፍ ያለበት በቀይና ጥቁር እስክሪፕቶ በሙሉ ገጽ ላይ የተሳለ የተወጋ ልብ አየ፡፡ገርሞት አስተምሮ ሲወጣ በሩ ጋ ጠርቶኝ

‹‹የማይፈቱት ባል ሞያ ብቻ ነው! ይሄ ፎንቃ የምትሉትን ነገር ትደርሺበታለሽ፡፡ መጀመሪያ በርትተሸ ተማሪ! እውነተኛ ፍቅር ከሆነ ደሞ አላማችሁን እስክታሳኩ ተጠባበቁ፡፡ ወርቅ በእሳት አንደሚፈተነው ፍቅራችሁ በጽናት መፈተን አለበት!›› ብሎኝ ሔደ፡፡

‹‹እውነቱን ነው!››

‹‹ምን ያደርጋል ልብ አርፍዶ ነው የሚመጣው! ከሶስት ወር በኋላ ነው የገባኝ፡፡ የአፈቀርኩት ልጅ ሆዴ እየገፋ ሲመጣ ሰበባሰበብ እየፈለገ እየተጣላኝ ሸርተት ሸርተት ማለት ጀመረ፡፡››

‹‹ምን የማይረባ ልጅ ነው!››

‹‹የማይረባ ብቻ፡፡ ልጅ ምናልባት ሃብት ነው፡፡ ሁሌ ችግሩ ሴቶችጋ ስለሚቀር ሴት ልጅ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለቴ ማሰብ ይጠበቅባታል፡፡ የት ትደርሳለች የተባልኩት ልጅ …››

መክብብ ‹‹ ጭፈራ ቤት ተገኘሽ!›› ሲል እንደገና ተሳሳቁ፡፡

‹‹ ኤችአይቪና ሌላ ነገር ስላልያሲያዘኝ ግን አመሰግነዋለሁ፡፡ በቃ ቤተሰቦቼ ዓይንሽ ለአፈር አሉኝ፡፡ በተለይ  በጣም ያስጠናኝ የነበረው አባቴ ያሰበልኝ ረዥም እቅዳችን በአጭር በመገታቱ ገና በልጅነቴ ሳልዳር በማርገዜ ክስተቱን ክብረ ነክ ጉዳይ አድርጎ ስለወሰደው አመረረ፡፡››

‹‹በእናንተ እድሜ ስሜትን መቆጣጠር ይከብድ ይሆናል፡፡ ግን ከቲቪና ሬዲዮ ከምትሰሙትም ኮንዶም ያልተፈለገ እርግዝናንና የጤና ጠንቅን ለመክላት ወሳኝ መሆኑን እንዴት ዘነጋችሁ፡፡››

‹‹አዎ ከቦይፍሬንዴ ጋር እንጦጦ ተራራ ላይ ሙዚየም ልናይ ሄደን ጀንበር ልትጠልቅ አካባቢ ተራራውን ስንወርድ አንድ በቋጥኝና በዛፍ የተሸፈነ ጨሌአማ ቦታ ሸርተት  አድርጎኝ ስንገዳገድ ወገቤን ይዞ አቆመኝ፡፡ ድንገት ነው ነገሩ የተከሰተው!አረግዛለሁ ብዬ አላሰብኩም››

‹‹ራስን ጠንካራ አድርጎ ኮንዶም መዘንጋት አይገባም!›› ሲል

‹‹አዎ ‹የቆመበት የቆመበትን አያውቅም!› አይደል የሚባለው፡፡››

አሪፍ አባባል ነው በሚል ሁኔታ ራሱን ነቅንቆ ‹‹ከዚያ ምን አደረግሽ? ልታስወርጂ ሞከርሽ?››  

‹‹ሠፈራችን የሆኑ ሴትዮ ጋር አስወርዳለሁ ብላ የሞተች ልጅ መኖሯን ገና ህፃን ሆኜ ስለሰማሁና ስላስበረገገኝ ያን አማራጭ አላሰብኩትም፡፡ ትምህርት አቋርጬ አያቴ ጋ ናዝሬት ሄጄ ወለድኩ፡፡ ነፍሰጡር እያለሁ በተፈጠረብኝ ቀውስ  እሳቀቅና እጨነቅ ስለነበር ሆዴን በመቀነት እሸብብ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት በልጁ ላይ መጠነኛ የአይምሮ ውሱንነት መኖሩን በቅርቡ እያስተዋልኩ ነው፡፡ ሐኪምም ይህን አረጋግጦልኛል፡፡›› ከጥቂት ሰከንድ ፀጥታ በኋላ

‹‹ልጄን ለስድስት ወር ከአጠባሁ በኋላ ለአያቴ ትቼው ሞጆ ሄጄ የቡና ቤት ሥራ ተለማመድኩ፡፡ከዚያ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ያሬድ ሙዚቃ አካባቢ…››

‹‹ ኢብሳ ህንጻ?››

 ‹‹አዎ እዛ ሠርቼ ወደ ካዛንችስ መጣሁ፡፡››

‹‹ለአያቴ ‹ሻይ ቤት ነው የምሰራው፡፡› እያልኩ ገንዘብ እልክላታለሁ፡፡››

‹‹እዚህ ሥራ ላይስ ምን ያህል ትጠነቀቂያለሽ?››

ጠቋሚ ጣቷን እያወዛወዘች

‹‹ሁለቴ መሸወድማ የለም፡፡ በጣም ነው የምጠነቀቀው!››

‹‹አዎ፣ በጣም ተጠንቀቂ ቻይናዎች ‹ጠዋት ያደናቀፈህ ድንጋይ ማታ ካደናቀፈህ ድንጋዩ አንተ ነህ!› ይላሉ ››

‹‹ ምን እሱ ብቻ ሌላው ሲደናቀፍ እያየህ አንተም ከተደናቀፍክም ያው ነው!››

‹‹ያዢ!›› ብሎ መክብብ ጽጌን ጨበጣት፡፡

‹‹ግን የሆነ ቀን በግዜ መጠጣት ጀምሬ ምግብ ቤት ጓደኛዬን ፍለጋ ስገባ አንድ በአርባዎቹ ያለ ጎልማሳ እራት ሲበላ ‹እንብላ!› ብሎኝ አብረን ራት ከበላን በኋላ ቢራ እንደ ጉድ አጠጣኝ፡፡ ከዚያ ‹ሌላ ቤት ሄደን እንጠጣ!› ሲለኝ አድርጌው የማላውቀውን ቀልቤ ደህና ሰው ነው የሚል ነገር ነግሮኝ ያለወትሮዬ ‹እሺ› አልኩት››

‹‹ መልክ ሌላ፣ ፀባይ ሌላ ምን ነክቶሽ ነው?››

‹‹አዎ፣ ፈርቼ ነበር፡፡.‹አይዞሽ! ሁለተኛ ዲቪዚዮን የሚባል ወመሾች ያሉበት ቤት ነው የምንሔደው!› ሲለኝ… ››

መክብብ ከት ብሎ ስቆ ‹‹ወጣት መሰል ሽማግሌዎች ማለቱ ነው!››

‹‹አዎ!››

‹‹ካዛንችስ ይገርምሻል ሁሉም አይነት  መጠጥ ቤት ነው ያለው! ለፍንዳታዎች ድንጋ መጣያ እስኪጠፋ ለእርቃን ሩብጉዳይ የሆነ አለባበስና ማራኪ ገላ ያላቸው ኮረዳዎች ግጥም የሚሉባቸው ጭፈራ ቤቶች፡፡ ሰከን ላሉት ደሞ ለስላሳ ሙዚቃና ረጋ ያሉ ምራቅ የዋጡ ሴት ወይዘሮ መሳይ አጫዋች ሴቶች ያሉባቸው ቤቶች አሉ፡፡››

‹‹አዎ የወሰደኝ ቤት እንደዚያ አይነት ቤት ስለሆነ ወድጄው ነበር፡፡አሁን ደሞ ውስኪ እንጠጣ ብሎ ደብል ደብል ውስኪ አዘዘ፡፡ ሞቅ እያለኝ መጣ፡፡የውስኪው ቃና ስላልተመቸኝ ወደቢራ ተመለስኩ፡፡››

 ‹‹ውይ ምን ነክቶሽ ነው? Whisky after beer is dear but beer after whisky is risky! ነው ፈረንጆች የሚሉት፡፡ ከውስኪ በኋላ ቢራ አደገኛ ነው ማለት ነው!››

‹‹መሆን አለበት መቀላቀል መጥፎ ነው! ክፍል እንድንገባ ሲጠይቀኝ ትዝ ይለኛል፡፡እኩለ ሌሊት ላይ ስባንን ከሆነ ሠው ጋ ማደሬን ሳውቅ ከአልጋው ላይ እመር ብዬ ተነስቼ ከራስጌዬ በኩል መብራት ዳብሼ አበራሁ!››

‹‹ ምን ለመፍጠር?››

‹‹ኮንዶም መጠቀሙን ለማወቅ ነዋ!››

‹‹ ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ!››

‹‹ ከግርጌ የተቀመጠ ፖፖ ውስጥ ኮንዶም መኖሩን ሳውቅ በጣም ደስ አለኝ፡፡››

‹‹ ሐላፊነት ከማይሰማው ሠውጋ አድረሽ ቢሆን አልቆልሽ ነበር!››

‹‹አዎ ግን በዛ አልረካሁም፡፡ ታውቃለህ ጫፍና ጫፉን ይዤ ኮንደሙ ውስጥ ያለውን ፈሳሽ አፍስሼ ምን አልባት ጫፉ ላይ ተበጥቶ እንደሆነ ብዬ ግማሽ ጠርሙስ ውሃ ስሞላበት ምንም አላፈሰሰም፡፡››

‹‹ ደስ አለሽ?››

‹‹ በጣም! ሰውየው ለካ የተኛ መስሎ የማደርገውን ይከታተል ነበር፡፡ ከት ብሎ ስቆ ‹አንቺ የሆንሽ ቡዳ ነሽ! ይሄን ያህል የምትጠነቀቂ ከሆነ መስከር አልነበረብሽም!› አለኝ፡፡ ስናወራ ነው ያደርነው፡፡ መቃምም ላልታሰበ ወሲብ እንደሚዳርግ ተስማምተን ጫትንም አወገዝነው!››

መክብብ እየሳቀ ‹‹ አሁን የምታወሪኝ ነገር ገግሩም ታሪክ ይወጣዋል!››ሲል

‹‹ አዎ ጻፈው፡፡ አየህ የዛእለት የገጠመኝ ሰው ክፉ አልነበረም፡፡ ከዚያእለት ወዲያ ግን  ላለመስከር እጠነቀቃለሁ፡፡ ያሬድ ሙዚቃ አካባቢ ሥሠራ አንድ ጓደኛዬ ጠዋት ላይ ‹ነይ ጥብስ ልጋብዝሽ!› ብላኝ  አንድ ኪሎ ለሁለት አዘን ከበላን በኋላ ኪሷ ስትገባ ማታ አብራው ያደረችው ሰውዬ ከሰጣት መቶ ሃምሳ ብር ላይ መቶውን ለካ ከቦርሳዋ አውጥቶ ወስዶታል፡፡››

መክብብ ጭንቅላቱን ይዞ ‹‹ምን አይነቱ ናዚ ነው የገጠማት!››

‹‹ታውቃለህ የሱን ጂን ከሷ ድራፈት ጋ ትንሽ ትንሽ እየቀላቀለ ነው ያሰከራት፡፡››

‹‹ወንዱም ሲሰክር ገንዘብ የሚዘርፉ ሴቶች አሉ!››

‹‹አዎ አሉ!››

‹‹ክው ብላ ስትደነግጥ ነገሩ ገብቶኝ ‹አይዞሽ ለአያቴ ልልከው የያዝኩት ገንዘብ አለ!› ብዬ ከነለስላሳው መቶ ሰላሳ ብር ስከፍል ‹ሃምሳ ብሩን ውሰጂ› ብትለኝ ‹እምቢ ሌላ ጊዜ ትሠጪኛለሽ!› አልኳት፡፡ምናልባት ሠክራ ኮንዶም ካልተጠቀመች ድንኳን ጃንሜዳ አካባቢ ዘርግተው ኤችአይቪ በነፃ የሚመረምሩ ግብረሰናይ ድርጅትጋ  ሄዳ ብትመረመር ጥሩ እንደሆነ አግባባኋት፡፡  በቅርቡ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ የቲቪ ቶክ ሾው ላይ አሁን በነገርኩህ ምክኒያት ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር እንደምትኖርና ‹በኛ ይብቃ ትውልድ ይዳን!› እያለች ስታስተምር ሰምቼ ደውዬ ‹በርቺ ጥሩ ልጅ ነሽ!› አልኳዋት፡፡››

‹‹የዛ ዕለት ሊሆን ይችላል ያሲያዛት! መስከር ወንድን ያለኮንዶም አንዲሄድ ያደፋፍራል፡፡ ሴትን ደሞ ያዘናጋል፡፡ከሁለቱም ጾታ አንዳንድ እኩዮች ምንአልባት ተይዘው ከሆነ በበቀለኛነት ስሜት ትውልድ ከማዳን ወደማጥፋት ሊያዘነብሉ ስለሚችሉ መጠንቀቅ ያሻል!››

አንድ ብርጭቆ ድራፍት ሲጠጣ የሚንበጫበጭ አብሾ ያለበት ድንክ ሰውዬ እየዞረ  ወንድ ጠጪዎችን ጉንጫቸውን ይስም ነበር፡፡ ወደ መክብብ ሲመጣ መክብብ ቶሎ ሊገላገለው ስለፈለገ ጉንጩን አቀበለው፡፡ እሱ እንደሄደ ጽጌ እማይረባ በሚል አይነት እጇን አወናጭፋ፣

‹‹አዎ ተጠንቅቀው እንኳን ኮንዶም  በአግባቡና በመመሪያው ካልተጠቀሙበት የሚበጠስበት  ወይ የሚሾልክበት አጋጣሚ ጥቂት አይደለም!››

‹‹ትክክል!››

‹‹አንዳንዱ ገልብጦ የሚያደርግ አለ፡፡ ሳይገለብጡትም በደንብ የማያጠልቁ አሉ ?ምን እሱ ብቻ የቆቡ ጫፍ ላይ ፣ለወንዱ ዘር መያዢያ እንዲሆን አየር አንዳይዝ ያዝ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አሊያ እንደፊኛ ተነፍቶ የሚበጠስበት እድል ብዙ ነው፡፡ የኮንደሙ ባኮ ላይ እኮ ማብራሪ አለ!››

 ‹‹አይደል! ግን ብዙ ሠው ያነበዋል ብለህ ነው? ››

‹‹አንድ ዓይናፋር ነርስ ስለኮንዶም ግንዛቤ ለማስጨበጥ ገጠር ሄዳ ትምህርት ስትሰጥ የእጇ አውራጣት ላይ ኮንዶም አጥልቃ ፊትዋን አዙራ አንዲህ አጥልቃችሁ አያለች አስተምራቸው ማታ ቤት ሲገቡ  ኮንደሙን አውራጣታቸው ላይ እያደረጉ ነበር ከሚስቶቻቸው ጋር ፍቅር የሰሩት የሚባል ቀልድ አለ››

ጽጌ  በሳቅ ጦሽ ብላ ‹‹ይገርማል ምትሃታዊ ነገር መስሎአቸው እኮ ነው፡፡ ውሸት ይሆናል ብለህ አታስብ፡፡ ግንዛቤ አስጨባጩም ወሳጁም በግልጽ በኮንዶም ዙሪያ ሊወያይ ይገባል፡፡ ኮንዶም መጠቀም ከሞራል ውጪ እንደሆነ ተደርጎ መታየት የለበትም፡፡ ሰውም ኮንዶም ለመግዛት፣ ለማጥለቅና ለመጣል ማፈር አይገባውም!›› አለች፡፡

መክብብ ቢራ ሲቀዳላት አንገቷን ሰበር አድርጋ አመስግና

‹‹ጊዜው ያለፈበት ኮንዶምም ሊበጠስ ይችላል!›› ስትል

መክብብ ጭንቅላቱን በአወንታ እየወዘወዘ

‹‹አዎ ግን ግዜ ያለፈባቸው ኮንደሞችን እንኳን  እንደ ህይወት ትረስትና ሴንሴሽን አይነት ጥራት፣ ምቾትና ግሩም መአዛ ያላቸው ኮንዶሞች የሚያስመጡት ዲኬቲዎች ከየኪዮስኩና ከየሱቁ እያደኑ እንደሚቀይሩዋቸው በሆነ ወቅት ሱቅ ወረፋ ይዤ አይቼአለሁ!›› 

ጽጌ ‹‹የሥንቱን ሕይወት ታድገዋል፡፡ቫይረሱ ካልተገታ በጆሜትሪክ ፕሮግሬሽን ሊተላለፍ ይችላል!›› ስትል መክብብ እውነትም ጎበዝ ተማሪ ነበርሽ በሚል አድናቆትና ፍቅር በተሞላበት አተያይ ዓያት፡፡

‹‹ምንአልባት ለሙቀት፣ ለፀሃይ ብርሃን እንዲሁም ለእርጥበት ከተጋለጠ ኮንደም ሊበላሽ ይችል ይሆናል፡፡›› አለች

‹‹ልክ ነሽ ባኮው የተጎዳ ከሆነም ችግር ሊኖርበትም ይችላል! ምንም እንኳ አጋጣሚው ወደ ዜሮ ቢጠጋም ሲመረት እንደማንኛውም ምርት ችግር ያለበት አምልጦ ሊወጣ የሚችልም አይጠፋ ይሆናል፡፡››

‹‹በአለፈው ሳምንት አንድ ፍንዳታ ክፍል ከያዝን በኋላ ‹ኮንደሙን ቅባት ቀብቼ ነው የማደርገው!› ብሎ ተወዛገበኝ ‹ኮንደም እኮ አስፈላጊው ቅባት ተደርጎለት በጥራት ተዘጋጅቶ ሀገር ውስጥ ከገባም በኋላ በዲኬቲ ባለሙያዎች  ጥንካሬው በቤተ ሙከራ ተፈትሾ ነው የሚሰራጨው፡፡ አስረድተውናል!› ብለው አሻፈረኝ አለ ‹እንደሱ ከሆነ ኮንደሙ ሊሾልክ ስለሚችል ለህይወቴ ዋጋ ስለምሰጥ ያንተ መቶ ስላሳ ብር ለምን ጥንቅር ብሎ አይቀርም! ደሞስ ምንነቱ ያልታወቀ ቅባት ማህፀኔ ላይ ችግር ቢፈጥር› ብዬ ብሩን ፊቱ ላይ ወርውሬለት ልወጣ ስል አንቆ ያዘኝ››

‹‹‹ይቺናት ጨወታ!› አለ ጥላሁን፡፡ አትጮሂም ነበር? ጠጪው፣ባሬስታው ፖሊስ ይረባረቡበት አልነበር! አንዷን የሚቀጥለው ቤት አንድ ሰካራም አንቆ ሲይዛት አስይዛዋለች፡፡››

‹‹በደመነፍስ እልሃለሁ ተንጠራርቼ ሳያስበው አንድ ጥፊ መረግኩበት!››

‹‹ወንድ ነሽ!›› መክብብ ጽጌን ዳግም ጨበጣት፡፡ጽጌ ፈገግ ብላ

‹‹ምን ወንድነት አለ ብለህ ነው? ድመት ስታባርራት ማምለጫ ካጣች ነብር ነው የምትሆነው! ለአልጋ ክፍሏ ልጅ ‹አጃቡልን ጥሪልኝ!›  ‹አጃቡልን ጥሪልኝ!› ብዬ በሩን ስከፍት ድንጋጤ ሳይለቀው፣ ብሩን ሳይሰበስብ ሹልክ ብሎ ጠፋ፡፡››

 ‹‹አጃቡል ዛፉ፣ አንደጥንቸል ያንጠለጥለው ነበር፡፡››

‹‹አዎ ግርግር ሲነሳ ሶስቱን ባንዴ አንጠልጥሎ ነው ደጅ የሚወረውራቸው፡፡››

‹‹የነቃሽ ነሽ፡፡ ትጠነቀቂያለሽ! አንቺን ነበር ማግባት!››

‹‹እንደሱማ ከሆነ ከመጠቀም ወደመተማመን እንሻገር ነበር፡፡›› አናርገው በሚል ፍቅር አተያይ ተያዩ፡፡ መክብብ አንድ እጇን ለቀም አድርጎ

‹‹አዎ፣ መጥኖ ለመውለድ፣ ልጅ ለመቆጠብና ለማራራቅ ከፈለግን ደሞ ወደኮንዶም መመለስ ይቻላል! ታውቂያለሽ ከሌሎች መከላከያዎች ኮንደምን ለየት የሚያደርገው የጎንዮሽ የሆርሞን ችግር የለውም፡፡››

‹‹አዎ፣ እሱን ለመጠቀም ዶክተር ጋር መሄድም አያስፈልግም፡፡ ላቁምም ከተባለ ጣጣ የለውም!››

‹‹በኮንዶም መሥራት ትንሽ ምቾት የሚሸርፍ ቢመስልም  በአንጻሩ ምቾትን የመጨመር ባህሪ ያለው ይመስለኛል፡፡ግን ታውቂያለሽ ኮንዶም ቶሎ አንዳልጨርስ የሴቷንም ስሜት ለመጠበቅ፣ የእርካታ እድሜን ለማራዘም እንደሚረዳ ደርሼበታለሁ፡፡ከጓደኞቼ በርካታዎቹ የኔን ሃሳብ ይጋራሉ፡፡››

ጽጌ ጥፍሯን እየበላች‹‹ባለጎድኑ ልዩ ምቾት አለው!›› አለች

‹‹አንዳንድ ሴቶች ደሞ ኮንደሙ ውስጥ ገብቶ የሚቀር  እየመሰላቸው ተሳቀው የሚያሳቅቁ አሉ!››

 ‹‹ኧረቴ ይሄው እንደ ጌጤ እዚህ ቦታ ይሄን ያህል ዓመት የሠሩ አንደሱ ሆነብኝ ያሉ ሴቶች አላጋጠሙኝም፡፡ ከስጋት የተነሳ ኮንዶም እንደርብ የሚሉም ከሁለቱም ጾታ አሉ፡፡ ይሄ እንኳን አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡››

‹‹በዲኬቲ ተመርምረው ገበያ ላይ የዋሉ ቀኑ ያላለፈባቸው ሴንሴሽንና ህይወት ትረስት ኮንዶሞች በቂ ናቸው፡፡››

‹‹ሜንበርስ ኦንሊ የሚልም ልዩ ማሸጊያ ያለው ትንሽ ወደድ የሚል የዲኬቲ ኮንደም የሚጠቀም ባለመኪና አጋጥሞኛል!››

‹‹የመአዛና የማሸጊያው ጥራት ካስከተለው የዋጋ ልዩነት በስተቀር ጥራት ላይ ልዩነት የላቸውም፡፡ ዲኬቲዎች ሴፍቲ ወይ ደህንነት ላይ እንደማይደራደሩ ስለማውቅ ሁሉም በቀላሉ ገዝቶ የሚጠቀምባቸውን ሴንሴሽንና ህይወት ትረስትን ነው እኔ እንኳ የምጠቀመው!››

‹‹አዎ፣ ለየት ማለት ከተፈለገ የሶስት ብር ሻይ  ሌላጋ በሃያ ብር መጠጣት ይችላል!››

‹‹መብት ነው!››

በጨዋታቸው መሃል  ሰውነቷን ከእርቃንነት የታደገ ብትቶ የለበሰች አስር ዓመት ያልሞላት ልጅ ተጠግታ ማስቲካ እንዲገዙዋት ስታግባባቸው መክብብ ልጅቷን ስለአሳዘነችው አንድ ባኮ ስተሮበሪ ገዝቶ ለጽጌ ሰጣት፡፡   

‹‹ሴቶች ክፍል የምታወሩትን ብሰማ ደስ ይለኝ ነበር! መቅረጫ ልስጥሽ እናንተኮ ተመራማሪ ጭምር ናችሁ፡፡ ››

‹‹ታዲያ፣ አንድ ፒያሳ አካባቢ ቡና ቤት ያላት ሴት ኬሚካል በመጠቀም  ጥቅም ላይ የዋሉ ኮንዶሞች ባኞ ቤትና ቱቦ እንዳይዘጉ ለማስወገድ የሚረዳ ዘዴ ፈጥራ መሸለሟን የውጪ ሚዲያን ጠቅሶ አንድ ዘጋቢ ዜና ሲያቀርብ መስማቴን አስታውሳለሁ! ታውቃለህ ሕጻናት ቢያገኙት ጥሩ አይመጣም መጫወቻ መስሎአቸው …››

‹‹አዎ፣ ልክ ነሽ ጥቅም ላይ የዋለ ኮንዶም አወጋገዱ ሊታሰብበት ይገባል!››

‹‹ዲኬቲዎች ወይ በኤችአይቪ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ከነገሯችሁ ውጪ ስለኮንደም የምታውቂው ነገር ካለ  እስቲ አጫውቺኝ፡፡ በምርምር ዓለም ኢምፕሪካል የሚባል ነገር አለ በምርምር ሳይሆን በልምድ የሚገኝ››

‹‹ አዎ፣ ኬሚስትሪ ስንማር ኢምፕሪካል ፎርሙላ የሚል ነገር ትዝ ይለኛል፡፡ ልክ ነህ  ቢዝነስ ሲጠፋ የክብሪት ቀፎ የምታህል የሴቶች ክፍል ውስጥ ተደራራቢ አልጋ ላይ ተደራርበን ነው የምንተኛው፡፡ ስናወራ ወንዱ ስሜቱን ጨርሶ በዚያው ከቀጠለ፣ አንዳንድ ሴቶች ደሞ ከገንዘብ ችግር የወር አበባቸው ሙሉ ለሙሉ ሳይሄድ ተጣጥበው ሲሰሩ  ኮንደሙ ሊበጠስ እንደሚችል ሃሳብ ተቀያይረናል፡፡ ››

‹‹ አሁን ላነሳሺው ነገሮች መረጃ ቢፈለግ ጓደኛዬን አንደማስረጃ ማቅረብ እችላለሁ፡፡ ታውቂያለሽ መጀመሪያ ሥራ የገባ ሰሞን አንድ  ማታ ማታ ተማሪ ለመምሰል ደፍተር ይዛ መንገድ ላይ የምትቆም ልጅ ‹የማታ ተማሪ ነኝ!› ብላው ተዋውቀው ጋብዟት ለቅባት ብር ሰጥቷት ‹ዛሬ ዝግጁ አይደለሁም ሌላ ቀን!› ስትል እንዳታመልጠው ስለጓጓ ‹በኮንዶም እናድርግ ብሏአት!› አብረው ገብተው  ኮንደሙ አሁን ባልሺያቸው ሁለት ምክንያቶች ተበጥሶ በማግስቱ ከሠዓት በኋላ ብልቱ አካባቢ የመቆጥቆጥ የመለብለብ ስሜት ተሰማው፡፡ በነጋው ሽንት መሽናት አቅቶት ነጭ ፈሳሽ ያንጠባጥብ ገባ፡፡ ታውቂያለሽ ደሞዙ ትንሽ ነበረች፡፡ ሁሉንም ቦታ ቦታ አሲዞ በቀረችው ነበር የተዝናናባት፡፡››

ጽጌ አየሳቀች‹‹ ጉድ ሆነአ!››  አለች

‹‹አዎ፣ ለመታከሚያ ገንዘብ አጥቶ ተቸግሮ ከኔ ተበድሮ ነው የታከመው፡፡ ደግነቱ ኤችአይቪ አልያዘውም፡፡ ጬብጡ ደሞ በቀላሉ ጠፋለት!››

‹‹አንዳንዱ ደሞ ኮንደሙ በግድ ይበጠስልኝ የሚል ይመስል  ወሲብን የወትድርና ስልጠና የሚያስመስለው አለ!››

መክብብ ፈገግ ብሎ ‹‹ አገላለጽሽ ይገርማል! እንደዛማ መሆን የለበትም በወሲብ ዙሪያ እውቁ ተመራማሪ ከማሳቱራ The Perfumed Garden በሚለው መጽሃፉ ወሲብ የስሜት ጣቢያዎችን የመፈለግና የመነካካት ጥበብ ስለሆነ በዝግታ መከናውን እንዳለበት ያስረዳል፡፡ አይፈጥረው የለ እንዲሉ በአንዳንድ አጋጣሚ የወንዱ በጣም ትልቅ፣ የሴቷ በጣም ጠባብ ከሆነ ኮንደሙም እንደ ሃገሩ አማካኙ ታስቦ ከሆነ የሚሰራው ምናልባት ሊበጠስበት የሚችልበት አጋጣሚ ካለ ረጋ ማለቱ አይከፋም!››

ጽጌ  ቢራ ተጎንጭታ ‹‹ትክክል! መፋቀር እኮ መታገል አይደለም! በአንድ ወቅት ጓደኛዬ ሺሻ ቤት ወስዳኝ፣ በደላሎች በኩል በስልክ እየተጠራች ትላልቅ ሆቴሎች ቢዝነስ የምትሰራ ልጅ የምራብ አፍሪካ ወንዶች መጠኑ ከኛ ወንዶች ከፍ እንደሚል ስታወራ ሰምቼአለሁ›› አለች፡፡

ጌጤ ሁለቱን ጃንቦ ድራፍት ይዛ መጥታ ‹‹ይቅርታ አስኪቀየር እኮ ነው የቆየሁት!›› ብላ አንዱን መክብብ ፊት አስቀምጣ አንዱን ግማሽ ድረስ ጭው አድርጋ ጠጥታ አጠገባቸው ቁጭ አለች፡፡ መክብብ የጌጤን ታሪክ መስማት ስለፈለገ

‹‹እሺ ጌጤ አንድ ልጅ ነው ያለሽ?››

‹‹ አዎ››  

‹‹ሴት ነች፣ ወንድ?››

‹‹ ሴት ነች! ትንሽ አመም ያደርጋታል! ሳስመረምራት ‹ጃርዲያ ነው!› ›› አሉኝ

‹‹ ከባልሽ እንዴት ተለያያችሁ?››

‹‹ሲቡ ስሬ ነበር የምንኖረው፡፡ ልጄን ለመውለድ የሚያርሰኝ ስለሌለ ወደ አንቦ እናቴ  ጋር መጥቼ ወልጄ ከክርስትና በኋላ ድንገት ቤቴ ስመለስ ሠራተኛዬ አልጋችን ላይ ተኝታ እሱ ደሞ ሶፋ ላይ ተኝቶ ደረስኩ፡፡››

‹‹ምንድነው?›› ብዬ ግራ በተጋባ ፊት ባሌን ጠየኩት

 ‹‹ልቧን አሟት ነው! አልጋው ይሻላታል ብዬ ነው!›› አለኝ፡፡

‹‹ግን ሁኔታውን ሳጣራ ከሱ አርግዛ አስወርዳ አንደሆነ ተገነዘብኩ፡፡ ሲሻላት አባርሬያት  አንድ ቀን ተዘጋጅቼ እሱ ሥራ ሲሄድ የምፈልገውን እቃ በሎንችና ጭኜ  አምቦ ወደናቴ ቤት አጓጓዝኩት፡፡››

ጽጌ በንዴት ‹‹ ወንዶች! ‹የቆመበት የቆመበትን አያውቅም!› ቢባልም ምነው እንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ እራሱን ፣ሚስቱን አንዲሁም ልጁን ከሚዶል ኮንዶም ቢጠቀም?›› አለች፡፡

 ‹‹ልክነሽ ጽጌ፣ ሃላፊነት የሚሰማው ሰው እንኳን ዘሩን ምራቁን የሚያኖርበት ስፍራ ይመርጣል!›› ብላ ፊቷን ኮሶ አስመስላ

‹‹ ደደብ ነው ተዉት! ልጄን ለእናቴ አደራ ብዬ አዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ ቡና ቤት ገባሁ!››

‹‹ አባቷ አይቆርጥላትም?››

 ‹‹ከሶስት ዓመት በኋላ አፈላልጎ አግኝቶኝ ‹ጫት ቅሜ መርቅኜ እኮ ነው !እባክሽ እንደገና አብረን እንሁን !›ቢለኝ ‹እንቢ እንዴት አምንሃለሁ ብዬ ሳይሆን  ለምን አምንሃለሁ ብዬ ነው!›  አልኩት ትንሽ ብር ይልካል፡፡ ሲቡ ሲሬ የእርሻ ጣቢያ ሠራተኛ ነው፡፡››

ጽጌሬዳ‹‹ ወንድን ማመን ቀብሮ ነው! ግን እኮ መልካም ወንዶች እንዳሉ በአንጻሩ አስቸጋሪ ሴቶችም ሊኖሩ ይችላሉ!›› አለች፡፡

እንዲህ እንዲህ እያሉ ሲያወጉ፣ ከውጭ የመጡና ውስጥ የሚደንሱ የፍንዳታ ቡድኖች ተጋጭተው ብርጭቆ መወራወር ሲጀመር ጽጌና ጌጤ

 ‹‹ እናምልጥ እናምልጥ!››

ብለው ወደኋላ በር ሲሮጡ መክብብ በደመነፍስ ተከተላቸው፡፡ ለሰከንድ ዘግይቶ ቢሆን ከግድግዳ ተላትሞ የተመለሰ የድራፈት ብርጭቆ ለይሕወቱ አሳዛኝ እልባት ያበጅለት ነበር፡፡

ጌጤ ተንደርድራ ሽንት ቤት ገብታ በሩን ስትቆልፍ፣ ጽጌ ክንፍ ያላት ይመስል በፍጥነት  ላይ ወደቤርጎ የሚወስደውን ቀጭኑን ደረጃ ሰከንድ በማይሆን አፍታ ወጣችው፡፡ መክብብ ከረብሻው ይልቅ ጽጌ እንዳታመልጠው ያሰበ ይመስል አሷ ወደምትሄድበት አቅጣጫ ነበር የሚያቀናው፡፡

አልጋ ክፍሏ ‹‹ኤጭ! ዛሬም ረብሻ ነው?  አጃቡል ሱቅ ሄዶ ነው?› ስትል ተደባዳቢዎች የኋለኛውን በር ገነጠሉት፡፡

ጽጌ ‹‹ና!›› ብላ መክብብን አንዱ ክፍል ጎትታ አስገብታው በሩን ቀረቀረች፡፡ አልጋ ክፍሏ ሌላኛው ክፍል ገብታ ቆለፈች፡፡ መክብብ ጽጌን

‹‹ አደገኛ ህይወት ነው የምትመሩት!›› ሲላት

‹‹አዎ ያሳዝናል የሻይ ቤት አስተናጋጅ መሆን እፈልጋለሁ! ኤድስን ያልተፈለገ እርግዝናን የአባለዘርና የሄፒታይተስ በሽታን በኮንዶም መቆጣጠር ይቻላል፡፡ ከንደዚህ አይነት ያልታሰበ ሞት ግን እንዴት ታመልጣለህ? አራት ኪሎ የሆነ ቡና ቤት የምትሠራ  ዘመድ የሌላት ምስኪን ልጅ በጥጋበኞች የተወረወረ ጩቤ ወግቷት ደመከልብ ሆና ቀርታለች፡፡››

‹‹አይዞሽ ጽጌ! እኔም እዚህ ከምመጣ ቤት ተከራይተን ተመርምረን አብረን መኖር እንችላለን፡፡ አንቺ የኔ ከሆንሽ ከነልጅሽ እቀበልሻለሁ!››

ብሎ ፊቷን ዳበስ ዳበስ ሲያደርጋት ደረቱ ላይ ልጥፍ ብላ አልጋው አጠገብ  የተሰየመውን ኮመዲና አየች፡፡

‹‹አልጋ ክፍሏ ምን ነክቷት ነው? ኮንዶም አላስቀመጠችም!›› ስትል

መክብብ ከደረት ኪሱ ኮንዶም ሲያወጣ  ፊቷ አንደፈንዲሻ ፈክቶ ጽጌ

‹‹ጎበዝ! ከየት አመጣኸው?›› ስትል

‹‹ ዛሬ እናቴን ላሳክም ክሊኒክ ሄጄ ነበር፡፡ወረፋ ለሚጠብቁ ሰዎች ከተዘጋጀ ማረፊያ ክፍል ጎን የፈለገ ወይ ከሱቅ መግዛት የሚፈራና የሚያፍር ሰው በነጸነት እንዲወስድ በሳጥን ተቀምጦ  ስለነበር የህይወት ስንቅ ስለሆነ አንዳላከስራቸው ፈርቼ ሶስት ባኮ ብቻ ዘገንኩ! አንዱን ቤት፣ አንዱን ቢሮ፣ አንዱን ይሄው አንደምታይው ኪሴ አስቀመጠኩት፡፡ ምነው እንደውጪ ድርጅቶች  በመሥሪያቤቶችም በየመጸዳጃ ክፍሉ ቢቀመጥ፡፡ ‹ረጅም ጦር ባይወጉበት ያስፈራሩበት!› አይደል የሚባለው›› ብሎ ካርቶኑን ከፍቶ ኮንደሙን ሲያወጣ

‹‹ቀስ ብለህ ጫፉ ላይ ቅደድና አውጣው፡፡ ጥፍርህ ወይ ጥርስህ እንዳይበጣው፡፡ ና ደሞ ላግዝህ፡፡ ሳይነቃ ብታጠልቀው ዋጋ የለውም!››