ያ የከንፈር ማህተም

ያ የከንፈር ማህተም

ከዚህ አለም ተለይተህ
ፀጥ ረጭ ብለህ
ከፊቴ ተዘርግተህ ሳለህ
አልሞከርኩም ምንም
የማይላወሱ ከንፈሮችህን ልስም !

ላይ በአፀዳ ነፍስ ሆነህ
ያሳለፍናቸውን የፍቅር ዓመታት አስበህ
ይሆን ታዝበህ?

ወስደህ ይሆን ግምት
ስታገኘኝ ያለወትሮዬ ጭምት
በጣቶቼ ጫፍ እንኳ
የወደድኩትን የማልነካ?
ግና በመጨረሻ ስትስመኝ
ታስታውስ ይሆን ምን እንዳልከኝ?

ውሰጅ ይህን
የከንፈር ማስታወሻ
ተቃርቧል የኔ መጨረሻ!”

በፍቅራችን የጨለማ ሰዓት
ምልክት ይሁንሽ ምናልባት
መልሰሽ እስክትሰጪኝ
አንድ ብሩክ ጠዋት ስታገኚኝ!”
ያልዳበስኩ ለዚያ ነው!
ግን እንዳልከው
ወደኋላ ተመልሼ
መልእክቱን አስታውሼ
ያን የመሰነባበቻ የከንፈር ማህተም
ልክ ከንፈሬ ላይ እንዳሳረፍኩ
ከነግለቱº¬ ነውየምዘልቀው!

(ጁሊያን ካርሎሊን,

Advertisements