ተራራው ጫፍ ከቀትር በሁዋላ

ከፀሃይዋ ስር፣

እሆናለሁ

ደስተኛ ፍጡር፣

ኣቻልባ በንጽጽር!

መቶ አበባዎች ብዳብስም፣

አንዲት እንኳን

አልቀጥፍም!

እንዲሁም፣ በመደመም፣

እመለከታለሁ

ኮረብታውን ደመናውን፣

ሲያስጎነብሰው ንፋሱ ሳሩን፣

ሲነሳ ሳሩ ተራውን!

በዚያ ድቅድቅ፣

ከተማዋ ከሩቅ

በመብራት ስታሸበርቅ፣

ብዙም ሳልጠብቅ፣

ጠንቅቄ የኔን መንደር፣

እጀምራለሁ ቁልቁል መንደርደር!

(ሴንት ቪኒሰንት ሚሌ Translation Alem Hailu)

Advertisements