መርዛማው ዛፍ

መርዛማው ዛፍ

 

በጓደኛዬ ተናድጄ ነበር

ምሬቴን እንደተነፈስኩ፣

ከብስጭት ተገላገልኩ!

 

በባላንጣዬ ተናድጄ ነበር

ምሬቴን ስለአፈንኩት፣

አጎነቆልኩት!

 

የፍርሃት እንባ ያለፋታ፣

አጠጣሁት ቀንና ማታ፣

የሽርደዳ ፈገግታ እያሞቅኩት፣

ኣጸደቅኩት፣ወደ ሸረብኩት

ወጥመድም

ባላንጣዬን ጋበዝኩት!

 

እየተመዘዘ ቀንና ማታ፣

ፍሬ አፈራ  ግሩም ለእይታ!

ጠላቴ የኔ መሆኗን እያወቀ፣

በፍሬዋ ውበት ተሰረቀ!

 

እናም ጭለማን ተገን አርጎ፣

ገባ ከአትክልት ስፍራዬ ሰርጎ!

 

በማለዳ ተመለከትኩ

በደስታ በአንክሮ፣

ጠላቴ ዛፏ ስር ተዘርሮ!

 

(በዊሊያም ብሌክ፣ትርጉም ዓለም ኃይሉ—-›በቀል የእግዚአብሔር ነው መሆን ያለበት ፣የኛ መሆን የለበትም!)

 

Leave a comment