ባልቴቷ ሱሳን

ባልቴቷ ሱሳን

ሱሳን  ሁሌ ሥራዋን ሰራርታ፣

ሲሻት እፎይታ፣

ትቀመጣለች ወፈር ያለ

ሻማ አብርታ፣

ባለግሩም መአዛውን

የማታ አየር በደንብ ለመሸመት፣

መስኮቷን አርጋው ከፈት!

ቦታው እንዳይጠፋባት

አልባ በአውራጣት

ተመስጦ በሚስተዋልበት

ኮስታራ ፊት

እየተደመመች ታነባለች

ዓይኗ እንደ ሸማኔ መወርወሪያ

ከዚህ ወደዛ ፣ወደዚህ ከዚያ

በመፅሃፉ ላይ  እያደረገች ሸርተት ፣

ሻማዋን ንፋስ እየታገላት!

በዛ ኮሽታ አልባ ፀጥታ፣

ይሰማል በለሆሳስ ስትናገር፣

የሆነ ነገር!

ወይ ጭንቅላቷን ነቅንቃ ስታበቃ

‹‹ምን አይነት ናችሁ፣

እንዴት እነደዚህ ታደርጋላችሁ!››

አይሰማም ምንም ድምፅ

ከሩቅ ሥፍራ አውራ ዶሮ ካልጮኽ

ወይ ወረቀት ሲገለፅ!

በትልቁ መነፅሯ ልታይ ዙራ

ሥፍራውን ማትራ

ሽበት ቀመስ ጭንቅላቷን

እየነቀነቀች ወደኔ እያየች

‹‹አንተ ገና አልተኛ ህም ?››ትለኛለች

ዳግም ወደ መፅሃፏ ተመልሳ

በሰመመን እራሷን ልትረሳ!

(በዋልተር ዲላ ሜር፣ ትርጉም ዓለም ኃይሉ)

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s