ቀበጧ ፅጌረዳ

           ቀበጧ ፅጌረዳ

እንቡጥ ፅጌረዳ አንገቷን ሰገግ አርጋ፣

ብቅ አለች ከአትክልቱ ሥፍራ በአበቦቹ አልጋ፣

አፍላ የወጣትነትን ወራት፣

የሚያጅበው የትኩስ ደም  ኩራት፣

በቃ አፍነከነካት!

ከጎኗ አትክልተኛውን ቆሞ ስታስተውል፣

የሃሳብ ብርቅታ ኣላት ውል-

‹‹አርጅቷል-በጣም አርጅቷል

በቅርቡ ይሞታል!››

 

ሞቃታማው የበጋ አየር ስለተስማማት፣

ክንፎቿን ዘርግታ በስፋት፣

ምንም ለመደበቅ ሳትዳዳ፣

ከፈተች የልበቧን ጓዳ!

ስትሰማ የእግሩን ኮቴ እንደገና

አሳቃት ደና- ‹‹አርጅቷል፣ አፍጅቷል

ብዙ ሰንብቷል አሁንስ ይሞታል!››

 

ግና የማለዳው ንፋስ ደርሶ፣

ስፍራውን አተራምሶ፣

ሲሄድ ተጣድፎ

አስተዋለ የፅጌረዳ ክንፍ

በአትክልቱ ቦታ ተነስንሶ!

 

ቀትር ላይ አዛውንቱ አትክልተኛው፣

ሁሉንም በሹካው፣ሰብስቦ ከላው!

 

እናም በዚህ ጉዳይ ስለተመሰጥኩ፣

የስንኝ ቋጠሮ ከተብኩ!

 

እኔ እንደአስተዋልኩት

ፅጌረዳዋ የውበትን

አትክልተኛው የጊዜን

ምስል ነው የሚከስቱት

 

(በአውስቲን ዶብሶን፣ትርጉም ኣለም ኃይሉ, ከፎንቴሌ የተወሰደ)

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s